የሩሲያ እና ሱዳን ግንኙነት ከፍተኛ ደረጃ ላይ እንደሚገኝ በሞስኮ የሀገሪቱ አምባሳደር ተናገሩ አምባሳደር ሞሐመድ ሲራጅ በስፑትኒክ እናት ኩባንያ ሩሲያ ሴጎንድኒያ ዋና መሥሪያ ቤት በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ባደረጉት ንግግር፤ የሱዳን ልዑካን ቡድን በቅርቡ ሩሲያን ጎብኝቶ ከሩሲያ የኢነርጂ ሠራተኞች ጋር መገናኘቱን አስታውሰዋል። ስብሰባው ፍሬያማ እነደነበርም ዲፕሎማቱ አጽንኦት ሰጥተዋል። የሱዳን ኢነርጂ እና ነዳጅ ሚኒስትር ሙህዪዲን ናኢም ሰኢድ በህዳር ወር አጋማሽ ላይ ከነዳጅ ኩባንያ አስተዳዳሪዎች ጋር በመሆን ሩሲያን ጎብኝተዋል። ሚኒስትሩ ከሩሲያ አቻቸው ሰርጌይ ሲቪሌቭ ጋር በጋራ ፕሮጀክቶች ላይ ስለተከናወኑ ጉዳዮች መወያየታቸውን፤ የሩሲያ ኢነርጂ ሚኒስቴር አስታውቋል።ዜናውን በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፡- APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia