የታንዛኒያ ገዥ ፓርቲ ቻማ ቻ ማፒንዱዚ በዚህ ሳምንት በተካሄደው የአካባቢ ምርጫ በከፍተኛ ድምፅ አሸነፈ

የታንዛኒያ ገዥ ፓርቲ ቻማ ቻ ማፒንዱዚ በዚህ ሳምንት በተካሄደው የአካባቢ ምርጫ በከፍተኛ ድምፅ አሸነፈ በመጪው ዓመት ከሚካሄደው ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ በፊት የሀገሪቱን የዲሞክራሲ ተቋማት መፈተሻ ተደርጎ የተቆጠረው እና እሮብ የተካሄደዉ የድምጽ አሰጣጥ በምርጫ ማጭበርበር ክሶች እና የአመፅ ክስተቶች የታዩበት ነበር። ታንዛኒያ ከፍተኛ ስልጣን የሚያሳድሩ ከ80,000 በላይ የአካባቢ መሪዎችን መርጣለች። የፕሬዚዳንት ሳሚያ ሱሉሁ ሀሰን ሲሲኤም ከ98% በላይ እንዳስመዘገበ እና 18 ሌሎች ፓርቲዎች ቀሪ መቀመጫዎችን መጋራታቸውን ይፋዊ ውጤቶች አሳይተዋል። "እነዚህ የተመረጡ አመራሮች በአስቸኳይ ቃለ መሃላ ሊፈፅሙ ይገባል" ሲሉ ምርጫውን የመሩት የመንግሥት ሚኒስትር ሞሐመድ ምቼንገርዋ ውጤቱን ይፋ ሲያደርጉ ተናግረዋል። ምርጫው በሚቀጥለው ጥቅምት ከሚካሄደው ፕሬዝዳንታዊ እና የፓርላማ ምርጫ በፊት ለፕሬዝዳንት ሀሰን የመጀመርያው ፈተና ነው።ዜናውን በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፡- APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
Sputnik