ጁባላንድ ከሶማሊያ ፌደራል መንግሥት ጋር የነበራትን ግንኙነት በይፋ አቋረጠች አህመድ ሞሐመድ እስላም ማዶቤ በከፊል ራስ ገዟ ጁባላንድ ፕሬዝዳንት ሆነው ሰኞ እለት በድጋሚ ተመርጠዋል። የፌደራል መንግሥት ምርጫውን በመቃወም ማዶቤ ላይ የእስር ማዘዣ ያወጣ ሲሆን፤ ጁባላንድም በተመሳሳይ ፕሬዝዳንት ሀሰን ሼክ ሞሐሙድ ላይ የእስር ማዘዣ አውጥታለች። "የጁባላንድ መንግሥት ከሶማሊያ ፌዴራል መንግሥት ጋር ያለውን ግንኙነት እና ትብብር በይፋ እና ሙሉ በሙሉ አቋርጧል" ሲል የክልሉ መንግሥት ማስታወቁን የምዕራቡ ዓለም የዜና አውታር ዘግቧል። ቀደም ሲል ጁባላንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ሃምዛ አብዲ ባሬ ወደ ኪስማዮ ሊያደርጉት የነበረውን ጉብኝት ሰርዛለች። ባሬ፤ ከጁባላንድ ምርጫ በፊት በፕሬዝዳንት ሀሰን ሼክ ሞሐሙድ እና በፕሬዝዳንት አህመድ ማዶቤ መካከል ንግግር ለያመቻቹ እንደነበር ተገልጿል። በጁባላንድ እና በሶማሊያ ፌዴራል መንግሥት መካከል ውጥረት የነገሰው፤ ጁባላንድ የራሷን የምርጫ ኮሚሽን ማቋቋሟን ተከትሎ ሲሆን፤ ሞቃዲሾ እርምጃውን አውግዛለች። ጁባላንድ ማዕከላዊ መንግሥቱ ሕገ-መንግሥታዊ ሥልጣኑ አልፏል ስትል ትከሳለች።ዜናውን በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፡- APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia