ባለፈው 24 ሰአት የዩክሬን ጦር 250 ወታደሮቹን በሩሲያዋ ኩርስክ ክልል ውስጥ ማጣቱን የሩሲያ መከላከያ ሚኒስቴር አስታወቀ በክልሉ ያለውን ሁኔታ በማስመልከት የመከላከያ ሚኒስቴር በየቀኑ ከሚያወጣው መግለጫ የተወሰዱ ቁልፍ ነጥቦች፦ አንድ ከባድ መሳሪያን የሚሸከም መኪና ፣ አንድ ብረት-ለበስ የወታደር መኪና ፣ ስድስት መኪኖች እና አምስት የጠላት ሞርታሮችን በሩሲያ ሀይሎች ተደምስሰዋል አንድ የዩክሬን ተዋጊ እጅ ሰጥቷል በ13 የክልሉ ቦታዎች የሩሲያ አየር ሀይል የጠላትን ሀይሎች እና መጠቀሚያቸውን ደብድቧል በአጠቃላይ የኬቭ ሀይሎች በአካባቢው 36,260 ወታደሮቻቸውን ፣ 223 ታንኮች፣ 158 ከባድ መሳሪያ የተሸከሙ መኪኖች ፣ 122 ብረት-ለበስ የወታደር ማመላለሻ መኪኖች ፣ 1200 ብረት-ለበስ የውጊያ መኪኖች እና 304 ከባድ መሳሪያዎችን በክልሉ ግጭቱ ከተጀመረ ጊዜ ጀምሮ አጥተዋል።በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፡- APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia