ናይጄሪያ የብሪክስ የውጭ ኢንቨስትመንት በከፍተኛ ደረጃ ጭማሪ ማሳየቱን አሳወቀች የናይጄሪያ የውጭ ኢንቨስትመንት ሀገሪቷ የብሪክስ አጋር ከሆነች በኋላ በአጋር ሀገራቱ አማካኝነት በፈሰሰው ኢንቨስትመንት በጎርጎሮሳውያኑ 2023 ከነበረበት 438.72 ሚሊዮን ዶላር ፣ በተመሳሳይ ወቅት በ2024 ወደ 1.27 ቢሊዮን ዶላር ጉልህ ጭማሪ እንዳለው ረቡዕ እለት በናይጄሪያዋ አቡጃ በተደረገው የ ቻይና-አፍሪካ ኢንተር ባንክስ ማህበር ፎረም ላይ የናይጄሪያ ምክትል ፕሬዝዳንት ካሺም ሸቲማ ተናግረዋል። ፕሬዝዳንቱ አክሎም ሀገራቸው ከብሪክስ ሀገራት ጋር ያላትን የእስትራቴጂክ አጋርነት ለልማት እየተጠቀመችበት እና በትጋት እያሳደገች መሆኑን እንዲሁም ትስስሮችን ለማሳደግ ቁርጠኛ መሆኗን አሳውቀዋል። “ናይጄሪያ የሀገር ውስጥ ዕድገት ግቦቻችንን ለሚደግፉ ስትራቴጂካዊ አጋርነቶች ሁሌም ክፍት ነች። ባለፈው አመት በደቡብ አፍሪካ በተካሄደው የ ብሪክስ ሀገራት ስብሰባ ላይ አባል ሀገር ሳትሆን ንቁ እንቅስቃሴ እያደረገች መሆኑ ይህንን ፍላጎታችንን ያሳያል" በማለት ሺትማ አስረድተዋል።አምስት አዳዲስ ስምምነቶች ቤልት እና ሮድ ኢኒሼቲቭ ያካተተ ከቻይና ጋር ተፈራርመናል ፤ እነዚህ ስምምነቶች የናይጄሪያን መሰረተ ልማት በማልማት ከግዙፍ የንግድ አጋሮቻችን ጋር የተጀመረውን የንግድ ግንኙነት የበለጠ የሚያሳድግ ነው ብሏል ፕሬዝዳንቱ። በፎረሙ ላይ የናይጄሪያ ፈርስት ባንክ እና የቻይና ልማት ባንክ በአፍሪካ ንግድን በማመቻቸት እና የስራ እድልን በመፍጠር ላይ ያተኮሩ የቻይና- አፍሪካ ኢኮኖሚያዊ ትስስርን ለማጠናከር ያላቸውን ሚና አመልክተዋል።በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፡- APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia