ደቡብ አፍሪካ የጂ-20 ሊቀመንበርነት ምርጫ ላይ ማሻሻያ እንዲደረግ ግፊት እያደረገች ነው ሲሉ ጂ-20ን እንዲያስተባብሩ የተሾሙት ዲፕሎማት ተናገሩ ደቡብ አፍሪካ በጎርጎሮሳዊያኑ ታህሳስ 1 የፕሬዝዳንትነቱን ቦታ የምትረከብ መሆኑን ተከትሎ የጂ-20 ሊቀመንበርን ለመምረጥ የሚያስችል አዲስ አሰራር ተግባራዊ ማድረግ አስፈላጊ መሆኑን በቡድኑ አጀንዳ ላይ ለማቅረብ አቅዳለች ፤ ሲሉ የደቡብ አፍሪካ የውጭ ጉዳይ እና የፋይናንስ ሚኒስቴሮች የጋራ መግለጫ ላይ ዲፕሎማቱ ማሶትሻ ሙንጉኒ መግለጻቸውን የሩሲያ ሚዲያ ዘግበዋል። የG-20 ህብረት ባደጉት ሀገራት እና በደቡባዊው አለምን በሚወክሉት በማደግ ላይ ባሉ ሀገራት መካከል መመጣጠን ሊኖር እንደሚያስፈልገው በአጽንዖት ገልጸዋል። በጎርጎሮሳዊያኑ የ2025 የጂ-20 ጉባዔን በጆሃንስበርግ የምታካሄደው አፍሪካዊቷ ሀገር በፕሬዚዳንትነቷ ወቅት የአፍሪካን እና የደቡባዊው አለምን ድምፆችን ለማጉላት አቅዳለች። ይህ ለማሻሻያ የሚደረገው ጥረት በጂ-20 ውስጥ በማደግ ላይ ያሉ ሀገራት ውክልና እና ተፅዕኖ እንዲጨምር ያለውን ፍላጎት ያመላክታል ሲሉ ዲፕሎማቱ ጠቁመዋል። የጂ-20 ሀገራት አሁን በአምስት ቡድኖች ተከፍለዋል። እያንዳንዱ ቡድን ከቡድኑ አባላት መካከል በዙር ለአንድ ዓመት ለቡድኑ ሊቀመንበር ይመርጣል። ለምሳሌ ደቡብ አፍሪካ ከሩሲያ፣ ከህንድ እና ከቱርክ ጋር በአንድ ቡድን ውስጥ ትገኛለች።በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፡- APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia