የህዳር 18 ረፋድ ዓበይት የአለም ዜናዎች፦ የዩክሬን ቀዉስ "በዉጊያ አውድማ" ላይ የነበረው ሁኔታ ማስረጃ መሰረት ከፖለቲካ እና ዲፕሎማሲ መፍትሄ እርቆ ነው በማለት የሩሲያው የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሰርጌ ላቭሮቭ ተናገሩ። የሩሲያ አየር መከላከያ ሲስተም በሩሲያ ግዛት ላይ ጥቃት ሊፈፅሙ የነበሩ 22 የዩክሬን ሰው አልባ አውሮፕላኖችን ጥቃት ከመፈፀማቸው በፊት ደመሰሳቸ። በእስራኤል እና ሊባኖስ መሀከል የተኩስ አቁሙ ተግባራዊ መሆን ጀመረ። ሪፖርቶች እንዳሉት የተኩስ አቁም ስምምነቱ ወደ ተግባር ለመግባት ከአንድ ሰአት በታች ሲቀረው ጭምር የእስራኤል አየር ሀይል በደቡባዊ ቤሩት ዳርቻዎች ተደጋጋሚ የአየር ድብደባ እየፈፀመ ነበር። የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ባይደን ኮንግረሱን ለዩክሬን ድጋፍ የሚሆን እና ለፔንታጎን ተመላሽ የሚሆን ተጨማሪ 24 ቢሊዩን ዶላር በሚስጥር መጠየቃቸው ተሰማ ጥያቄው በመጪው ታህሣሥ የሚታሰቡበት ይሆናል። የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላዲሚር ፑቲን "ካዛኪስታንካያ ፕራቫዳ" ተብሎ ለሚጠራው ጋዜጣ "ሩሲያ - ካዛኪስታን: ወደፊቱን ለመስራት በህይወት የተደረገ ጥምረት" በሚል ርእስ መጣጥፍ ፃፉ።በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፡- APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia