በኮፕ29 ለአየር ንብረት ለውጥ ምላሽ የተመደበው 300 ቢሊዮን ዶላር በቂ አይደለም ሲሉ በማደግ ላይ ያሉ ሀገራት ተቹ

በኮፕ29 ለአየር ንብረት ለውጥ ምላሽ የተመደበው 300 ቢሊዮን ዶላር በቂ አይደለም ሲሉ በማደግ ላይ ያሉ ሀገራት ተቹ ህንድ እና የአፍሪካ ሀገራት፤ ለአየር ንብረት ለውጥ የታቀደው የገንዘብ መጠን በማደግ ላይ ያሉ ሀገራት ከጠየቁት 1.3 ትሪሊዮን ዶላር ያነሰ ነው በማለት ተቃውሟቸውን አሰምተዋል። የህንድ ተደራዳሪ ቻንዲ ራይና "ህንድ የቀረበውን ግብ አትቀበልም። ለማሰባሰብ የተወሰነው መጠን በጣም አነስተኛ ነው። ጥቂት ገንዘብ ነው። ለአየር ንብረት ለውጥ በቂ ምላሽ እንድንሰጥ የሚያስችል አይደለም" ማለታቸውን ጠቅሶ፤ ዘ ኢንዲያን ኤክስፕረስ ዘግቧል። የአፍሪካ ልዑካን ቡድን መሪ አሊ ሞሐመድም፤ በስምምነቱ ደስተኛ እንዳልሆኑ ገልጸዋል። "ባኩ ውስጥ ስምምነት ላይ ለመድረስ ዝግጁ ነን፤ በጣም ከፍ ያለ ስምምነት ላይ መድረስ አለብን፤ ሆኖም ቀይ መስመሮቻችንን የሚያልፉ ነገሮችን ለመቀበል ዝግጁ አይደለንም" ብለዋል የአፍሪካ ልዑካን ቡድን መሪው።ዜናውን በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፡- APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiop
Sputnik
በኮፕ29 ለአየር ንብረት ለውጥ ምላሽ የተመደበው 300 ቢሊዮን ዶላር በቂ አይደለም ሲሉ በማደግ ላይ ያሉ ሀገራት ተቹ ህንድ እና የአፍሪካ ሀገራት፤ ለአየር ንብረት ለውጥ የታቀደው የገንዘብ መጠን በማደግ ላይ ያሉ ሀገራት ከጠየቁት 1.3 ትሪሊዮን ዶላር ያነሰ ነው በማለት ተቃውሟቸውን አሰምተዋል። የህንድ ተደራዳሪ ቻንዲ ራይና "ህንድ የቀረበውን ግብ አትቀበልም። ለማሰባሰብ የተወሰነው መጠን በጣም አነስተኛ ነው። ጥቂት ገንዘብ ነው። ለአየር ንብረት ለውጥ በቂ ምላሽ እንድንሰጥ የሚያስችል አይደለም" ማለታቸውን ጠቅሶ፤ ዘ ኢንዲያን ኤክስፕረስ ዘግቧል። የአፍሪካ ልዑካን ቡድን መሪ አሊ ሞሐመድም፤ በስምምነቱ ደስተኛ እንዳልሆኑ ገልጸዋል። "ባኩ ውስጥ ስምምነት ላይ ለመድረስ ዝግጁ ነን፤ በጣም ከፍ ያለ ስምምነት ላይ መድረስ አለብን፤ ሆኖም ቀይ መስመሮቻችንን የሚያልፉ ነገሮችን ለመቀበል ዝግጁ አይደለንም" ብለዋል የአፍሪካ ልዑካን ቡድን መሪው።ዜናውን በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፡- APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia