ህንድ ከኢትዮጵያ ጋር የኢኮኖሚ ትብብሯን ማስፋት እንደምትፈልግ የሀገሪቱ አምባሳደር ተናገሩ

ህንድ ከኢትዮጵያ ጋር የኢኮኖሚ ትብብሯን ማስፋት እንደምትፈልግ የሀገሪቱ አምባሳደር ተናገሩ በኢትዮጵያ የህንድ አምባሳደር ሽሪ ሮበርት በማዕድን፣ ግንባታ እና በመሠረተ ልማት ትብብርን ለማሳደግ የሚያስችሉ ትልቅ ዕድሎች እንዳሉ፤ ከኢትዮጵያ መንግሥት መገናኛ ብዙሃን ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ ጠቅሰዋል። የህንድ ኩባንያዎች ኢትዮጵያ ውስጥ ጠንካራ የሁለትዮሽ አጋርነት እንደፈጠሩ እና በብዛት እንደሚገኙም ጠቅሰዋል። ፎስፎረስ፣ ብረት እና ወርቅን ጨምሮ የኢትዮጵያ ያልተነካ የማዕድን ሀብት የህንድ ኢንቨስትመንት ዋነኛ ትኩረት ነው ብለዋል። ህንድ፤ በኮንስትራክሽን እና በከተማ ልማት ከኢትዮጵያ ጋር በሰፊው መተባበር እንደምትፈልግም አምባሳደሩ ጠቁመዋል። ኢትዮጵያ እያካሄደች ያለው የኢኮኖሚ ማሻሻያ ዋና የኢንቨስትመንት ማዕከል እንደሚያደርጋት የተናገሩት አምባሳደሩ፤ ሀገሪቱ ከዓለም ዙርያ ኢንቨስትመንት እንድትስብ ያስችላታል ብለው እንደሚያምኑ ገልጸዋል።ዜናውን በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፡- APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
Sputnik
ህንድ ከኢትዮጵያ ጋር የኢኮኖሚ ትብብሯን ማስፋት እንደምትፈልግ የሀገሪቱ አምባሳደር ተናገሩ በኢትዮጵያ የህንድ አምባሳደር አኒል ኩማር ራይ በማዕድን፣ ግንባታ እና በመሠረተ ልማት ትብብርን ለማሳደግ የሚያስችሉ ትልቅ ዕድሎች እንዳሉ፤ ከኢትዮጵያ መንግሥት መገናኛ ብዙሃን ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ ጠቅሰዋል። የህንድ ኩባንያዎች ኢትዮጵያ ውስጥ ጠንካራ የሁለትዮሽ አጋርነት እንደፈጠሩ እና በብዛት እንደሚገኙም ጠቅሰዋል። ፎስፎረስ፣ ብረት እና ወርቅን ጨምሮ የኢትዮጵያ ያልተነካ የማዕድን ሀብት የህንድ ኢንቨስትመንት ዋነኛ ትኩረት ነው ብለዋል። ህንድ፤ በኮንስትራክሽን እና በከተማ ልማት ከኢትዮጵያ ጋር በሰፊው መተባበር እንደምትፈልግም አምባሳደሩ ጠቁመዋል። ኢትዮጵያ እያካሄደች ያለው የኢኮኖሚ ማሻሻያ ዋና የኢንቨስትመንት ማዕከል እንደሚያደርጋት የተናገሩት አምባሳደሩ፤ ሀገሪቱ ከዓለም ዙርያ ኢንቨስትመንት እንድትስብ ያስችላታል ብለው እንደሚያምኑ ገልጸዋል።ዜናውን በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፡- APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia