ፑቲን የሩሲያ መከላከያ ሚኒስቴር አመራር የኦሬሽኒክ ሚሳኤልን በተሳካ ሁኔታ ሙከራ ላይ በማዋሉ አድናቆታቸው ገለጹ የሩሲያ ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን የኦሬሽኒክ ሚሳኤል ሙከራን አስመልክቶ ባደረጉት ንግግር ያነሷቸው ቁልፍ ነጥቦች፡- 🟠 የኦሬሽኒክ ስርዓት ክምችት አለ፤ ሩሲያ ስርዓቱን መሞከር ትቀጥላለች። 🟠 የኦሬሽኒክ ስርዓት የሶቪየት መሳሪያዎችን በማዘመን የተሰራ ሳይሆን፤ የአዲሲቷ ሩሲያ ባለሙያዎች የፈጠራ ውጤት ነው። 🟠 የኦሬሽኒክ ስራ ውጤትና ፍጥነት የሩሲያ የሮኬት ምህንድስና ዩንቨርስቲ የሩሲያን ሉዓላዊነት ለማረጋገጥ፤ ችግሮችን የመፍታት አቅም እንዳለው አሳይቷል፡፡ 🟠 የኦሬሽኒክ ስርዓት ለሩሲያ ሉዓላዊነት እና የግዛት አንድነት ተጨማሪ ዋስትና ነው፡፡ 🟠 የኦሬሽኒክ ስርዓት ከስልታዊ የጦር መሳሪያዎች ጋር ሊወዳደር የሚችል ነው፡፡ 🟠 ኦሬሽኒክ ሚሳኤል በብዛት እንዲመረትና ወደ ስልታዊ ሚሳኤል ሃይሎች እንዲደርስ ተወስኗል፡፡ 🟠 በአሁኑ ሰዓት የኦሬሽኒክ ሚሳኤልን ማጨናገፍ የሚችል ስርዓት የትም አይገኝም፡፡ 🟠 የኦሬሽኒክ ስርዓት ፈጣሪዎች እና ንድፍ አውጪዎች ለብሔራዊ ሽልማት ይታጫሉ። 🟠 ኦሬሽኒክ ኢላማውን በከፍተኛ ትክክለኝነት የሚመታ ሚሳኤል እንጂ፤ የጅምላ ጨራሽ መሳሪያ አይደለም፡፡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፡- ለአንድሮይድ ስልኮች በዚህ APK ፋይል ሊንክ ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia