ሁለት ታጣቂ ቡድኖች ትጥቃቸውን በመፍታት ለኒጀር ባለስልጣናት እጃቸውን ለመስጠት እንደተዘጋጁ ተዘገበ በርካታ ታጣቂዎች፤ በመጪዎቹ ቀናት ትግላቸውን ያቆማሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ዘገባዎች አመላክተዋል። እንደ የኒጀር መገናኛ ብዙሃን ዘገባ ከሆነ፤ ታጣቂዎቹ “ለአባት ሀገር ጥሪ” ምላሽ ለመስጠት የወሰኑ ናቸው። ታጣቂዎቹ፤ በመጀመሪያ ዙር ከጎረቤት ሀገር ወደ ኒጀር የሚገቡ እንደሆነ፤ የመገናኛ ብዙሃን ምንጮች ጠቁመዋል። ከህዳር ወር መጀመሪያ ጀምሮ፤ ከ12 በላይ የአማፂው የአርበኞች ነፃ አውጪ ግንባር የቀድሞ ተዋጊዎች፤ ለኒጀር ባለስልጣናት እጃቸውን ሰጥተዋል።ዜናውን በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፡- ለአንድሮይድ ስልኮች በዚህ APK ፋይል ሊንክ ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia