ማዳጋስካር የአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጠናን ተቀላቀለች የማዳጋስካር ብሔራዊ ምክር ቤት፤ የአፍሪካ ነፃ የንግድ ቀጠና ስምምነትን ሰኞ እለት ማጽደቁን ተከትሎ፤ ሀገሪቱ በዓለም ትልቁን ነፃ የንግድ ቀጠና መቀላቀል ችላለች።ከ1.2 ቢልዮን በላይ ህዝብ በሚይዝ ገበያ እና በ2.5 ትሪልዮን ዶላር አጠቃላይ የሀገር ውስጥ ምርት፤ ነጻ ቀጠናው ለአባላቶቹ ከፍተኛ ኢኮኖሚያዊ ጥቅም ያለው ትልቅ የንግድ እድል ነው ሲል፤ የማላጋሲ መንግሥት ተናግሯል። የአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጠና፤ ለበለጸጉ ሀገራት በ90% የታሪፍ መስመሮች የጉምሩክ ቀረጥን በ5 ዓመታት ውስጥ እንደሚወገድ፤ ለደሃ ሀገራት ደግሞ በ10 ዓመት ውስጥ እንደሚነሳ ያስቀምጣል።ዜናውን በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፡- ለአንድሮይድ ስልኮች በዚህ APK ፋይል ሊንክ ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia