ዋሽንግተን ለዩክሬን መንግስት በሩሲያ ግዛት እንዲጠቀም በፈቀደችው የረጅም-ርቀት ሚሳኤልን በተመለከተ ከሩሲያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የተሰጠ ተጨማሪ መግለጫ ዩክሬይን የምእራባውያን ረጅም-ርቀት ሚሳኤል በሩሲያ ግዛት ላይ የምትጠቀም ከሆነ የግጭቱ ባህሪ ተቀይሮ ወደከፋ ደረጃ ይደርሳል። ሚኒስትሩ በመግለጫው አክሎም የኬቭ መንግስት የረጅም-ርቀት ሚሳኤሎችን በሩሲያ ግዛት ላይ የሚጠቀም ከሆነ አሜሪካ እና አጋሮቿ ከሩሲያ ጋር በቀጥታ በግጭቱ ተሳታፊ ይሆናሉ ብሏል። አሁንም ቢሆን የዩክሬን መንግስት የረጅም- ርቀት ሚሳኤሎችን በሩሲያ ግዛት እንድትጠቀም በአሜሪካን ፍቃድ ተሰጥቷቷል የሚለውን መረጃ እውነትነት የሞስኮ መንግስት አላረጋገጠም። ምንም አይነት ከምእራባውያን የሚሰጥ' ተአምራዊ መሳሪያ' በዩክሬን እየተደረገ ያለውን ልዩ ወታደራዊ ኦፕሬሽን አቋም አይቀይረውም።ዜናውን በእንግሊዝኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ ለአንድሮይ ስልኮች በዚህ APK ፋይል ሊንክ ስፑትኒክ ኢትዩጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia