የሩሲያ ጦር በዶንዬትስክ ህዝቦች ሪፐብሊክ የሚገኙትን የማካሮቭካ እና ሌኒንስኮ መንደሮችን እንደተቆጣጠረ የሩሲያ መከላከያ ሚኒስቴር አስታወቀ በሚኒስቴሩ ዕለታዊ መግለጫ የተነሱ ተጨመሪ ነጥቦች፡- 🟠 የሩሲያ ዩግ (ደቡብ) የጦር ሰራዊት ቡድን፤ ታክቲካል አቋሙን በማጠናከር 625 የሚደርሱ የዩክሬን ወታደሮችን ያስወገደ ሲሆን፤ ሁለት የመልሶ ማጥቃት ሙከራዎችን መልሷል። 🟠 ሚኒስቴሩ አክሎም ከሩሲያ ዛፓድ (ምዕራብ) ተዋጊ ቡድን ጋር በተደረገ ውጊያ፤ ዩክሬን 440 የሚደርሱ ወታደሮችን እንዳጣች እና የሩሲያ ወታደሮች ሁለት የመልሶ ማጥቃት ጥቃቶችን መልሰው፤ ሶስት የጥይት ማከማቻዎችን ደምስሰዋል ብሏል። 🟠 በተጨማሪም የዩክሬን ሃይሎች ከሩሲያ ቮስቶክ (ምስራቅ) ተዋጊ ቡድን ጋር በተደረገ ውጊያ፤ 140 የሚሆኑ ወታደሮችን እንዳጡ ሚኒስቴሩ አስታውቋል።ዜናውን በእንግሊዘኛ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፡- ለአንድሮይድ ስልኮች በዚህ APK ፋይል ሊንክ ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia