የኢትዮጵያ መዲና በ2017 በጀት ዓመት ከ30 በላይ ዓለም አቀፍ ዝግጅቶችን እንዳስተናገደች የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ገለጸ በተለይም፤ 46ኛው የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ እና ዓለም አቀፍ የሐይማኖት ተቋማት ጉባኤ፤ በአዲስ አበባ መካሄዱን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ነብያት ጌታቸው ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ አንስተዋል። ባለሥልጣኑ አክለውም፤ በሩሲያ ሲሪየስ ፌዴራላዊ ግዛት በተካሄደው የሩሲያ-አፍሪካ አጋርነት ፎረም የሚኒስትሮች ኮንፈረንስ፤ የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ከሌሎች የአፍሪካ ሀገራት ተወካዮች እና ከሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌ ላቭሮቭ ጋር ውጤታማ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት እንደነበራቸው ተናግረዋል። የ2017 የኢትዮጵያ በጀት ዓመት በጎርጎርያን ካላንዳር ሐምሌ 7፣ 2024 ጀምሯል።ዜናውን በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፡- ለአንድሮይድ ስልኮች በዚህ APK ፋይል ሊንክ ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia