የቻይና ኩባንያዎች በኢትዮጵያ በተመረጡ የኢኮኖሚ ዘርፎች ላይ እንዲሰማሩ ጥሪ ቀረበ የቻይና ጂያንግሱ ግዛት ከፍተኛ የልዑካን ቡድን የተሳተፈበት የቻይና-አፍሪካ የኢኮኖሚ እና የንግድ ትብብር ጉባኤ ትናንት አዲስ አበባ ተካሂዷል።በጉባዔው ላይ ንግግር ያደረጉት የገንዘብ ሚኒስትሩ አሕመድ ሽዴ፤ የኢትዮጵያ እና ቻይና ግንኙነት ወደ ላቀ ደረጃ እየተሸጋገር መሆኑን ገልጸዋል። ኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ማሻሻያ ማድረጓን የገለፁት ሚኒስትሩ፤ በዚህም ምቹ የኢንቨስትመንት ዕድል መፈጠሩን ተናግረዋል። የቻይና ኩባንያዎች ይህን ዕድል በመጠቀም መንግሥት ቅድሚያ በሚሰጣቸው ግብርና፣ ቱሪዝም፣ ቴክኖሎጂ እና ማዕድን ዘርፎች እንዲሰማሩ ጥሪ ማቅረባቸውን የሀገር ውስጥ መገናኛ ብዙሃን ዘግቧል።ምስሎቹ ከኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የማህበራዊ ትስስር ገጽ የተገኙ ናቸው መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፡- ለአንድሮይድ ስልኮች በዚህ APK ፋይል ሊንክ ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia