" ሩሲያ- ኢትዮጵያ : የምንጠብቀዉ ጊዜ የለም" የተሰኘ አለምአቀፍ የኢኮኖሚ ፎረም በአዲስ አበባ ተከፈተ ይህ ኮንፈረንስ በአፍሮኮም የአፍሪካ ሀገራት ኢኮኖሚ ጉዳዩች አስተባባሪ ፤ በሩሲያ የንግድ ማህበረሰብ እና በሮስኮንግረስ ፋውንዴሽን ትብብር የተዘጋጀ ነው። ይህ ኮንፈረንስ አላማ ያደረገው ለሩሲያ እና ለኢትዩጵያ የንግድ ማህበረሰብ አባላት በጋራ ጥቅም ላይ የተመሰረተ የትብብር መድረክ መፈጠር እና የሩሲያን ምርቶች እና ቴክኖሎጂዎች ለአፍሪካ ገበያ ማስተዋወቅ ነው። "እዚ የመጣነው ውጤታማ ስለሚሆኑ ፕሮጀክቶች ለማውራት ብቻ አይደለም ፤ አጋሮችን ለማግኘት ጭምር ነው። የሩሲያ ቢዝነስ ፕሮጀክቶችን እና ስታርትአፖችን መፍጠር ላይ የሚረዳን አጋር እንፈልጋለን። ይህም በብሪክስ ጉባኤ ወቅት የሩሲያው ፕሬዝዳንት እና የኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚኒስተር ያወሩበት እና ያበረታቱት ጉዳይ ነው" በማለት የአፍሪኮም ሰብሳቢ ኢጎር ሞሮዞ ለስፑትኒክ ባልደረባ ተናግረዋል።ይህ ፎረም እስከ ህዳር አምስት ይቀጥላል። መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ ለ አንድሮይድ ስልኮች በዚህ APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia