ቻድ እና ሩሲያ በትምህርት እና ልማት ላይ ያላቸውን መተባበር እያጠናከሩ ነው የቻድ ባለስልጣን ከስፑትኒክ ጋር በነበራቸው ቃለ-መጠየቅ የቻድ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ተወካይ ፋቲም አልዲጂንህ ጋርፋ የአፍሪካ ሀገሮች ሩሲያ ጋር በተለይ በትምህርት በቴክኖሎጂ እና በግብርና ዘርፎች ጥልቅ የሆነ ትብብር እንዳላቸው ተናግረዋል። "የራሳችንን አህጉር አርክቴክቸር ፖሊሲ በራሳችን መንገድ ለመንደፍ እኛ አፍሪካውያን ከሩሲያ ጋር በጠረጴዛ ዙርያ ውይይት ማድረግ ያስፈልገናል።" በማለት ነበር ተወካይዋ በ #ሩሲያአፍሪካ የሚኒስትሮች ኮንፈረንስ ጎንዮሽ ላይ ለስፑትኒክ ተናግረዋል። "በትምህርት ዙሪያ የቻድ ዲፕሎማ በሩሲያ ተቀባይነት እንዲኖረው የሩሲያም በተመሳሳይ የሚል ስምምነት ተፈራርመናል" ይህ በትምህረት ዙሪያ ያደረገውን ጉልህ ስምምነት ነው። ይህ ስምምነት በሩሲያ እየተማሩ ያሉ የቻድ ተማሪዎችን እና የቻድን ከፍተኛ የትምህርት ተቋም በእጅጉ ይጠቅማል በማለት ተወካይ ሚኒስተሯ ጨምረዋል።ዜናውን በእንግሊዝኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ ለ አንድሮይድ ስልኮች በዚህ APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia