በጋዛ ሰርጥ እስራኤል እያካሄደች ባለችው ወታደራዊ ጥቃት የሟቾች ቁጥር 43,600 በለጠ የጤና ሚኒሰቴር " ካለፈው አመት መስከረም 26 ጀምሮ በእስራኤል ወረራ የሟቾች ቁጥር 43,603 ሲደርስ 102,929 ሰዎች ቆስለዋል። ባለፉት 24 ሰአታት የእስራኤል ጦር በጋዛ ሰርጥ ባደረገው የሶስት ቤተሰቦች የጅምላ ግድያ 51 ሰዎች ሲሞቱ 164 ቆስለዋል" በማለት የሚኒስቴሩ መግለጫ ያሰረዳል። አሁንም ድረስ የጥቃቱ ሰለባዎች በተደረመሱ ህንፃዎች ስር ይገኛሉ፤ የአደጋ ጊዜ ሰራተኞችም ሆነ የሲቪል መከላከያ ሀይሎች ሊደርሱበት በማይችሉበት ሁኔታ ነው ብሏል ሚኒስተሩ በመግለጫው። ዜናውን በእንግሊዝኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ ለ አንድሮይድ ስልኮች በዚህ APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia