ኡጋንዳን የብሪክስ አጋር ሀገር እንድትሆን ሩሲያ ድጋፏን ትሰጣለች የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ላቭሮቭ " በአለምአቀፍ ጉዳዩች ላይ ኡጋንዳ ያላትን ሚዛናዊ እና ገንቢ አቀራረብ አስተውለናል እናም አክብሮት አለን፤ ሀገራችሁ በአፍሪካ ህብረት ውስጥ በሱማሊያ፣ በደቡብ ሱዳን ፣ በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኦፍ ኮንጎ እና በአፍሪካ ትላልቅ ሀይቆች አካባቢ ያላትን የሰላም ማስከበር ጥረትን እናደንቃለን። ባለፈዉ ጥቅምት በነበረው የብሪክስ ጉባኤ ለሀገራት የማስፋፊያ ግብዣ ሲደረግ የኡጋንዳን እጩነት ሩሲያ ድጋፍ ሰጥታዋለች" ላቭሮቭ ይህንን ያሉት ከኡጋንዳ አቻቸው ጄጄ ኦዱንጎ ጋር በነበራቸው የ #ሩሲያአፍሪካ አጋርነት ፎረም ሚኒስትሮች ኮንፈረንስ ወቅት በነበራቸው የጎንዩሽ ስብሰባ ወቅት ነው።የብሪክስ አጋር መሆን የተለያዩ ምርጫዎች ያሉት ሲሆን ከሙሉ አባል ሀገራት ጋር አብሮ መስራትን እና ድምፅ ሰጥቶ ከመምረጥ ውጭ ያሉትን ሁሉንም መብቶች ያጎናፅፋለ። የሩሲያው ምክትል ውጭጉዳይ ሚኒስቴር ሰርጌ ረይበኮቭ በዚህ አመት መጀመሪያ ላይ እንዳሉት የብሪክስ አጋር ሀገር መሆን "ወደ ሙሉ አባልነት የተጠጋ ነው" ብለዋል።ዜናውን በእንግሊዝኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ ለ አንድሮይድ ስልኮች በዚህ APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia