አየርላንድ በእስራኤል ላይ የተከፈተውን የዘር ማጥፋት ክስ መቀላቀል እንደምትፈልግ ዘገባዎች አመለከቱ"ደቡብ አፍሪካ በእስራኤል ላይ የከፈተችውን የዘር ማጥፋት ክስ ለመቀላቀል የወሰንነው ጥንቃቄ የተሞላበት ጥልቅ የህግ ግምገማ ካደረግን በኋላ ነው" ሲሊ የአይሪሽ የውጭ ጉዳይ ሚኒስተር ሚካኤል ማርቲን በብሄራዊ ፖርላማ ስብሰባ ላይ መናገራቸውን የሀገር ውስጥ ሚዲያዎች ዘግበዋል።ደቡብ አፍሪካ ይህንን ክስ በእስራኤል ላይ የከፈተችው በጎርጎሮሳውያኑ አቆጣጠር በታህሳስ 2023 ነበር። ይህንንም ክስ የኒካራጓ፣ ፍልስጤም፣ ቱርክ፣ ስፔን፣ ሜክሲኮ፣ ሊቢያ፣ ኮሎምቢያ፣ ቺሊ፣ ማልዲቭስ እና ቦሊቪያ መቀላቀላቸውን ዓለም አቀፉ የወንጀል ፍርድ ቤት አስታውቋል።ዓለም አቀፉ የወንጀል ፍርድ ቤት በመጀመሪያ ደረጃ ውሳኔው እስራኤል የዘር ማጥፋትን የተመለከቱ ዓለም አቀፍ ስምምነቶችን እንድታከብር እና በጋዛ ላሉ ሲቪል ዜጎች የሚደረገውን የስብዓዊ እርዳታ መቀጠሉን እንድታረጋግጥ ጠይቋል።ዜናውን በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ ለ አንድሮይድ ስልኮች በዚህ APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia