ሩሲያ ለሉዓላዊነቷ ብቻ ሳይሆን ለሌሎች ሀገራት ነፃነትም ጭምር እየታገለች ነው ሲሉ ፑቲን ተናግረዋል "የምንታገለው ለኛ ነጻነት፣ መብት እና ሉዓላዊነት ብቻ እንዳልሆነ መናገር እንችላለን። ትግላችን ዓለም አቀፍ መብቶችና ነፃነቶች እንዲሁም የአብዛኞቹ ሀገራት ህልውና እና የመልማት እድል እንዲከበር ነው" ሲሉ በቫልዳይ የውይይት ክለብ ስብሰባ ላይ የተናገሩት የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን፤ ሩሲያ ከየትኛውም ሀገር ጋር ገንቢ ውይይት ለማድረግ ምንጊዜም ዝግጁ እንደሆነች ገልጸዋል። ለዓለም ስኬታማ እድገት፤ የሩሲያ ህልውና ቁልፍ እንደሆነም የሩሲያው መሪ አክለዋል። በተጨማሪም፤ የኒውክሌር ጦር መሳሪያ በሰው ልጅ ላይ ትልቅ ስጋት እንደደቀነ ፑቲን ተናግረዋል። "የኒውክሌር ኃይልን ለሰላማዊ አገልግሎት ከማዋል ባሻገር፤ የኒውክሌር ጦር መሳሪያዎች ለሰው ልጅ ትልቅ ስጋት ይፈጥራል" ያሉት ፑቲን፤ በተለይም የአየር ንብረት ለውጥን ለመጋፈጥ፤ ሰላማዊ የአቶም አጠቃቀም እየጨመረ እንደሚመጣ አስታውቀዋል።ዜናውን በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፡- ለአንድሮይድ ስልኮች በዚህ APK ፋይል ሊንክ ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia