"የአሜሪካ የአፍሪካ ፖሊሲ ከዚህ በኋላ ትርጉም የለውም" ሲሉ አፍሪካዊ ፕሮፌሰር ግምታቸውን አስቀመጡ

"የአሜሪካ የአፍሪካ ፖሊሲ ከዚህ በኋላ ትርጉም የለውም" ሲሉ አፍሪካዊ ፕሮፌሰር ግምታቸውን አስቀመጡ የአሜሪካ ምርጫ ብዙም አያስጨንቀንም። ከቅርብ ጌዜያት ወዲህ፤ አፍሪካውያን ምርጫውን ማንም ያሸንፍ ግድ አይሰጣቸውም፤ ሲሉ ናይጄሪያዊ የፖለቲካ ሳይንስ ኤክስፐርት ፕሮፌሰር ሸሪፍ ጋሊ ኢብራሂም ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል። አፍሪካውያን፤ የትራምፕ ወደ ስልጣን መምጣት ዩናይትድ ስቴትስ በአፍሪካ የምትከተለው ፖሊሲ ላይ ለውጥ ያመጣል ብለው አይጠብቁም፤ ያሉት ፕሮፌሰሩ፤ ለመቶ ዓመታት ወይም ክፍለ ዘመናት ከምዕራቡ ዓለም ጋር የነበረው ግንኙነት ለአፍሪካ ትርጉም ያለው እድገትም ሆነ ልማት አላስገኘም ሲሉ አክለዋል። አፍሪካ፤ ከዚህ በኋላ በምዕራባውያን መመዘኛዎች ደስተኛ እንዳልሆነች እና በዓለም አቀፍ ስርዓት ውስጥ የበለጠ ፍትሃዊ እና ሚዛናዊ መጪ ግዜን ትሻለች ሲሉ ተናግዋል። አፍሪካ፤ ሰላምና ትብብርን ከሚያበረታታው የብሪክስ ስርዓት ጋር አሰላለፏ እየጨመረ መምጣቱ፤ ለዚህ ማሳያ ነው ብለዋል። የትኛውንም የዩናይትድ ስቴትስ እጩ እንደማይደግፉ የገለጹት ፕሮፌሰር ኢብራሂም፤ ትራምፕ የዩክሬንን ግጭት እንደሚያስቆሙ በገቡት ቃል፤ ይህም በጋዛ ሰላም ለማምጣት አስፈላጊ ነው ብለው ስለሚያምኑ የተሻሉ አማራጭ ናቸው ብለው እንደሚያምኑ ገልጸዋል። ይሁን እንጂ በትራምፕ የስልጣን ዘመን ከቻይና ጋር ሊፈጠር የሚችለው የንግድ ጦርነት፤ በዓለም ኢኮኖሚ ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ ሊያሳድር እንደሚችል አስጠንቅቀዋል።ዜናውን በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፡- ለአንድሮይድ ስልኮች በዚህ APK ፋይል ሊንክ ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
Sputnik