የጥቅምት 28 ረፋድ አበይት የዓለም ዜናዎች፡-🟠 የሩሲያ ጦር በሀገሪቱ ቮሮኔዝ ክልል 14 እንዲሁም በቤልጎሮድ ክልል አንድ፤ በአጠቃላይ 15 የዩክሬን ሰው አልባ አውሮፕላኖችን ሌሊቱን መትቶ እንደጣለ የሩሲያ መከላከያ ሚኒስቴር አስታውቋል።🟠 የአሜሪካ ፕሬዝዳንታዊ እጩ ካማላ ሃሪስ፤ በምርጫው መሸነፋቸውን ተቀብለው፤ ለመጪው ግዜ እና ለአሜሪካ መርሆች ያሚደረጉትን ትግል እንደሚቀጥሉ ተናግረዋል፡፡🟠 የእስራኤል አየር ሃይል በሊባኖስ ቤይሩት ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ አቅራቢያ የሚገኘውን የኡዛይ አካባቢ ደበደበ፡፡🟠 የሩሲያ የድንገተኛ አደጋ ሚኒስቴር ልዩ በረራ፤ 24 ቶን ሰብዓዊ እርዳታ ቤሩት ማድረሱን የሚኒስቴሩ የፕሬስ አገልግሎት ዘግቧል።🟠 በኒውክሌር ሃይል ዘርፍ ቀዳሚ የሆነው የሩሲያ የምርምር እና ልማት ተቋም የኩርቻቶቭ ኢንስቲትዩት፤ ለሩሲያ መንግሥት የኢነርጂ ኮርፖሬሽን ጋዝፕሮም የውሃ ውስጥ የኒውክሌር ጋዝ ተሸካሚ ሊገነባ እንደሆነ፤ የማእከሉ ፕሬዝዳንት ሚክሂል ኮቫልቹክ ለስፑትኒክ ተናግረዋል።ዜናውን በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፡- ለአንድሮይድ ስልኮች በዚህ APK ፋይል ሊንክ ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia