ኢትዮጵያ የምግብ ሉዓላዊነቷን ለማረጋገጥ በትክክለኛ ጎዳና ላይ ነች ሲሉ ፕሬዝዳንት ታየ አጽቀሥላሴ ተገናሩ ፕሬዝዳንቱ አዲስ አበባ በተካሄደው "ከረሃብ ነፃ ዓለም" ጉባዔ ተሳታፊ የአፍሪካ ሀገራት መሪዎች፣ ሚኒስትሮችና የተቋማት ኃላፊዎች የእራት ግብዣ በተደረገበት ወቅት የተናገሩት ነው። ፕሬዝዳንት ታየ አጽቀ ሥላሴ በግዜው ባደረጉት ንግግር፤ ረሃብ በርካታ የአፍሪካ ሀገራትን የፈተነና ችግር ፈቺ መፍትሔ የሚሻ የጋራ ጉዳይ መሆኑን ተናግረዋል። ኢትዮጵያ፤ ረሃብ የሚያስከትለውን ጉዳት በጽኑ ትገነዘባለችም ያሉት ፕሬዝዳንቱ፤ ኢትዮጵያ የምግብ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ በሚያስችል ትክክለኛ መንገድ ላይ እንደምትገኝ ገልጸዋል። አክለውም፤ ኢትዮጵያ በስንዴ ራሷን ከመቻል ባለፈ ለውጭ ገበያ መላክ የሚያስችል አቅም መፍጠሯን ጠቅሰው፤ በዚህ ረገድ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እያበረከቱት ያለውን የመሪነት ሚና አድንቀዋል። መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፡- ለአንድሮይድ ስልኮች በዚህ APK ፋይል ሊንክ ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia