ትራምፕ በወሳኟ የኔቫዳ ግዛት 75% ድምጽ ቆጠራ ከተካሄደ በኋላ በ50.9% መምራት መጀመራቸውን አሶሺየትድ ፕሬስ ገልጿል ኔቫዳ ላሸናፊው ስድስት የወኪል ድምፆችን ታስገኛለች። ከ2000 እና 2004 በስተቀር፤ ከ1992 ጀምሮ ዲሞክራቶችን መርጣለች። በ2020 ምርጫ ጆ ባይደንን መርጣለች። በተጨማሪም፤ ትራምፕ በሌላኛዋ ቁልፍ ግዛት ፔንስልቬንያ ከ90% ድምጽ ቆጠራ በኋላ 51.2% በማግኘት መምራት ጀምረዋል። ተፎካካሪያቸው ምክትል ፕሬዝዳንት ካማላ ሃሪስ 47.8% አግኝተዋል። መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፡- ለአንድሮይድ ስልኮች በዚህ APK ፋይል ሊንክ ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia