የተባበሩት መንግሥታት ድርጀት የታዳጊ ሀገራትን ፍላጎት ያማከለ ውክልና ሊኖረው ይገባል ስትል ኢትዮጵያ አስገነዘበች ኢትዮጵያ፤ በሩሲያ ካዛን ከተማ የተካሄደው 16ኛው የብሪክስ የመሪዎች ጉባኤ ውጤት ዙርያ፤ በጀኔቫ የሩሲያ ፌደሬሽን ቋሚ መልዕክተኛ ባዘጋጀው ማብራሪያ መድረክ ላይ ተሳትፋለች፡፡ በመድረኩ የተሳተፉት በተመድ የጄኔቫ ቢሮ የኢትዮጵያ ቋሚ መልዕክተኛ አምባሳደር ጸጋአብ ክበበው፤ ዓለም አቀፍ ተቋማት የአስተዳደር መዋቅራቸው እንዲሻሻል እርምጃዎች መውሰድ አለባቸው ብለዋል። አክለውም፤ የተባበሩት መንግሥታት ድርጀት የታዳጊ ሀገራትን ፍላጎት ያማከለ ማሻሻያዎችን ማድረግ እንዳለበት ጠቁመዋል። በጄኔቫ የሚገኙ የብሪክስ አባል ሀገራት ቋሚ መልዕክተኞች በሰብዓዊ መብት፣ ንግድ፣ ጤና፣ ዲጂታል ቴክኖሎጂ እና አየር ንብረት ለውጥ ዘርፍ በትኩረት ለመስራት መስማማታቸውን፤ የሀገር ውስጥ መገናኛ ብዙሃን ዘግቧል። መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፡- ለአንድሮይድ ስልኮች በዚህ APK ፋይል ሊንክ ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia