የጥቅምት 26 ረፋድ ዋና ዋና የዓለም ዜናዎች፦

የጥቅምት 26 ረፋድ ዋና ዋና የዓለም ዜናዎች፦ 🟠 ሰሜን ኮሪያ 100 ኪሎ ሜትር ከፍታ እና 400 ኪሎ ሜትር ርቀት የሚሸፍኑ በትንሹ 7 ሚሳኤሎችን እንዳስወነጨፈች የጃፓን የመከላከያ ሚኒስቴር አስታወቀ። 🟠 የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንታዊ እጩዎች የመጨረሻ የምርጫ ቅስቀሳቸውን በአሜሪካ ወሳኝ ግዛቶች እያደረጉ ነው። ዶናልድ ትራምፕ በሚሺጋን ግራንድ ራፒድስ ከተማ ውስጥ የሚጠበቁ ሲሆን ካማላ ሃሪስ በፊላደልፊያ ለመራጮች ንግግር ያደርጋሉ። 🟠 የሩሲያ አየር መከላከያ ሃይሎች 6 የዩክሬን ሰው አልባ አውሮፕላኖችን ሌሊቱን አወደሙ። ድሮኖቹ በሩሲያ ብራያንስክ ክልል ላይ ተመተው መውደቃቸውን የሀገሪቱ መከላከያ ሚኒስቴር አስታውቋል።🟠 እስራኤል በሰሜን ጋዛ በሚገኝ ሆስፒታል ባደረሰችው ጥቃት ህጻናትን ጨምሮ በትንሹ 6 ሰዎች እንደቆሰሉ ዘገባዎች አመለከቱ። 🟠 ከቮስቴክኒ ኮስሞድሮም የተወነጨፈው "ኢኖስፌር-ኤም" ሳተላይት በተሳካ ሁኔታ ምህዋር ላይ ማረፉን የሩሲያ ስፔስ ኤጄንሲ ሮስኮስሞስ አስታወቀ።ዜናውን በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፡- ለአንድሮይድ ስልኮች በዚህ APK ፋይል ሊንክ ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
Sputnik