ማንነታቸው ያለታወቀ አጥቂዎች በሶማሊያ የአሜሪካና ዪናይትድ ኪንግደም ኤምባሲዎች በሚገኙበት አካባቢ የሞርታር ጥቃት ፈጸሙየሞርታር ጥቃቱ፤ የአሜሪካ እና የዩናይትድ ኮንግደም ኤምባሲዎች፣ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ተልዕኮ እና በሶማሊያ የአፍሪካ ህብረት የሽግግር ተልዕኮ አትሚስ ዋና መስሪያ ቤቶች የሚገኙበትን የሞቃዲሾ ሃላን አካባቢን ኢላማ ያደረገ መሆኑን ሶማሊ ጋርዲያን ዘግቧል።በጥቃቱ ሰለ ደረሰው ጉዳይ እስካሁን የታወቀ ነገር ባይኖርም በማህበራዊ ሚዲያ እየተሰራጩ ያሉት ምስሎች ከባድ ጉዳት መድረሱን አመላክተዋል።መረጃዎች እዳመላከቱት ከሆነ ጥቃቱ የተፈፀመው በአሸባሪው ቡድን *አልሸባብ ታጣቂዎች ነው።በኤክስ ማህበራዊ ትስስር ገጹ ባወጣው መግለጫ የሽብር ጥቃት መፈጸሙን በመግለጽ ድርጊቱን አወግዟል። ይሁን እንጂ ተጨማሪ መረጃ አልሰጠም።* ይህ አሸባሪ ድርጅት በሩሲያ እና በሌሎች በርካታ አገራት ታግዷል።ዜናውን በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ ለ አንድሮይድ ስልኮች በዚህ APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia