የብሪክስ ብድን ሀገራት ተለዋጭ የክፍያ ሰረአት እንዲዘረጋ እቅዱ ላይ ቅደመ ድጋፍ ማድረጋቸውን የሩሲያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አሳወቁ " ይህ አጀንዳ በካዛን በተደረገው የብሪክስ ጉባኤ እና በዚህ አመት በተደረጉ የፋይናንስ ሚኒስትሮች እንዲሁም የብሄራዊ ባንክ ገዢዎች ስብሰባዎች ላይ የነበረ ነው። የምንደግፋቸውን ሀሳቦች በንድፍ መልክ አስቀምጠናቸዋል። አላለቀም ነገርግን አስተማማኝ፣ ቀጣይነት ያለው እና ለረጅም ጊዜ የሚቆይ የክፍያ ስረአት እተዘረጋ ነው። እርግጠኛ ነኝ ቀጣይዋ የብሪክስ ሊቀመንበር የሆነችው ብራዚል የተጀመረውን ስራ እንደምታስቀጥለዉ። " ይህንን ያሉት የሩስያው የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሰርጌ ላቭሮቭ ከብሪክስ ቲቪ ጋር በነበራቸው ቃለ መጠየቅ ነው። የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ጨምረውም፦ ብሪክስ የራሱን የክፍያ ስረአት የሚዘረጋው ዶላርን በመጠቀም ከሚመጡ አደጋዎች ራሱን ለመጠበቅ ነው ተብለዋል። " የአሜሪካን ዶላር በአለም ኢኮኖሚ ውስጥ በስፋት እንደ ጦር መሳሪያ መጠቅሚያ እየሆነ ስለመጣ ስለሆነ ትይዩ የሆነ የገንዘብ ስረአት አስፈላጊ ነው። ቀጣይ ምን እንደሆነ ማንም አያውቅም። አሜሪካን አሁን ካለችበት ተስፋ አስቆራጭ አቋም አንፃር የዘፈቀደ አሰራሩ ከሚያመጣው መዘዝ የሚድን የለም። የበላይነታቸው በድንገት የሚቆም እና ነገሮች በፍጥነት እንደሚያልቁ ይሰማቸዋል ፤ ነገርግን ረጅም ጊዜ ነው የሚወስደው በዚህ ምክንያት ሁሉንም ነገር መጠቀም ይፈልጋሉ ፤ በጭራሽ የሚከለከለውን ማጠራቀም ጭምር " በማለት ላቭሮቭ ያስረዳሉ።ዜናውን በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ ለ አንድሮይድ ስልኮች በዚህ APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia