ጠቅላይ ሚኒስቴር ዐቢይ አህመድ ኢትዩጵያ የባህር በር ያሰፈልጋታል አሉየምስራቅ አፍሪካ ውጥረት እንደቀጠለ ነውየኢትዮጵያን የባህር በር ፍላጎት ላይ አፅንኦት የሰጡት ጠቅላይ ሚኒስቴር ዐብይ "በማንኛውም የህግ አግባብ ኢትዮጵያ የባህር በር ይገባታል " ብለዋል። ይሄ መግለጫ የወጣው የኢትዮጵያ መንግስት የባህር ሀይል መገንቢያ ለማግኘት ሱማሊያ ግዛቴ ናት ከምትላት ሱማሌላንድ ጋር የተፈራረመው ስምምነት ምክንያት በተፈጠረው ውጥረት መሀከል ነው። ጠቅላይ ሚኒስተሩ ሀገሪቷ ግጭት ውሰጥ የመግባት ምንም አይነት ፍላጎት እንደሌላት ገልፀው፦ ነገር ግን ገፍቶ የሚመጣ ካለ ራሷን ለመከላከል ዝግጁ መሆኗን አስረድተዋል። "ኢትዩጵያን ሊወሩ የሚችሉ የተወሰኑ ሀገራት እንዳሉ ሰጋት አለ ነገር ግን ማንም ሀገር ዝቅ አድርጎ ሊገምተን አይገባም። " ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይኤርትራ ከኢትዩጵያ ከተገነጠለች ካለፈው ሶስት አስርት አመታት ጀምሮ ሀገሪቷ የባህር በር አልባ ሆናለች። የሀገሪቱ የባህር ላይ ንግድም በጅቡቲ ላይ የተመረኮዘ ነው።ዜናዉን በእንግሊዝኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ ፦ ለአንድሮይድ ስልኮች በዚህ APK ሊንክ ፋይልስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia