ኢትዮጵያ ከአፍሪካ ትልቁን አየር ማረፊያ መገንባት እንደጀመረች ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ገለጹ

ኢትዮጵያ ከአፍሪካ ትልቁን አየር ማረፊያ መገንባት እንደጀመረች ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ገለጹ የኢትዮጵያ አየር መንገድ በአመት 100-130 ሚልዮን መንገደኞችን ማስተናገድ የሚችል ከአፍሪካ ግዙፉን አየር ማረፊያ እየገነባ እንደሆነ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መደበኛ ስብሰባ ላይ ተናግረዋል ሲል የሀገር ውስጥ መገናኛ ብዙሃን ፋና ዘግቧል። እንደ ዘገባው ከሆነ እየተገነባ ያለው አዲስ አየር ማረፊያ ከነባሩ አየር ማረፊያ ጋር በባቡር መንገድ ይገናኛል። የአፍሪካ ትልቁ አየር መንገድ የሆነው የኢዮጵያ አየር መንገድ በ124 አዳዲስ አውሮፕላኖች አገልግሎቱን እያስፋፋ የአፍሪካ የአቪየሺን ማእከል መሆኑን ቀጥሏል። እንደ ፋና ዘገባ አየር ማረፊያው የጥገና እና ሌሎች አገልግሎቶችን በማስፋፋት የስራ እድሎችን እየፈጠረ እና አገልግሎቱን እያጠናከረ ይገኛል። የግንባታ ዜናው አየር መንገዱ "የአፍሪካ ምርጥ" በመባል በ2025 አፔክስ የመንገደኞች ምርጫ ከተሸለመ በኋላ የመጣ ነው። አየር መንገዱ በተለያየ ዘርፎች ማለትም በበረራ ላይ መስተንግዶ፣ መዝናኛ፣ ምግብ እና መጠጥ፣ የመቀመጫ ምቾት እና በገመድ አልባ ኢንተርኔት አገልግሎቱ ባሳየው የተሻለ አፈጻጸም ተሸልሟል።ዜናውን በእንግሊዝኛ ያንቡብ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ ለአንድሮይድ ስልኮች በዚህ APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዩጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
Sputnik