የ #BRICS2024 የመሪዎች ጉባኤ የካዛን መግለጫ አፍሪካን በተመለከተ ያነሳቸው ቁልፍ ነጥቦች፦ 🟠 "ለአፍሪካውያን ችግሮች አፍሪካዊ መፍትሄዎች" መርህ በአፍሪካ ውስጥ ግጭቶችን ለመፍታት መሰረት ሆኖ ሊያገለግል ይገባል። 🟠 መግለጫው በመካከለኛው ምስራቅ እና በሰሜን አፍሪካ አካባቢ ያለው አለመረጋጋት የሚፈጥረውን አደጋ አጽንኦት ይሰጣል። 🟠 የአፍሪካ ህብረት በአፍሪካ ግጭቶችን በመከላከል፣ በመቆጣጠር እና በመፍታት ረገድ ወሳኝ ሚና ይጫወታል። 🟠 በአፍሪካ ቀንድ እና በሳህል የሚገኙ ሀገራት ሽብርተኝነትን ለመከላከል የሚያደርጉት ጥረት በከፍተኛው የሚመሰገን ነው። 🟠 የአፍሪካ አልማዝ ማዕድን ማውጫ ሀገሮችን የሚያሳትፈው መደበኛ ያልሆነ የብሪክስ የትብብር መድረክ መፈጠር የጥሬ አልማዝ ነፃ ንግድ እና የዓለም አቀፉ የአልማዝ ኢንዱስትሪ ዘላቂ ልማትን በማረጋገጥ ረገድ በመልካም ጎኑ ይወሰዳል። 🟠 ያላደጉ ሀገራት በተለይም የአፍሪካ ሀገራት በዓለም አቀፍ ሂደቶች ንቁ ተሳትፎ እንዲያደርጉ መግለጫው ጥሪ ያቀርባል። መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፡- ለአንድሮይድ ስልኮች በዚህ APK ፋይል ሊንክ ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia