ማሌዢያ በሩሲያ ላይ ለተጣለው የአንድ ወገን ማዕቀብ እውቅና አትሰጥም ሲሉ የግብርና ሚኒስትሩ አስታወቁ "ሩሲያ እና ኢራን ማዕቀብ የተጣለባቸው ሀገራት ናቸው፤ ማዕቀቦቹ በተለየ መልኩ የአንድ ወገን ማዕቀቦች ናቸው፤ ማሌዢያ በአንድ ወገን ለተጣለ ማዕቀብ እውቅና አትሰጥም ሲሉ የማሌዢያ የግብርና እና የምግብ ዋስትና ሚንስትር ሞሃመድ ሳቡ ለስፑትኒክ ተናግረዋል።ሚኒስትሩ አክለውም ማሌዢያ ከሩሲያ ጋር የጠበቀ ግንኙነት ለመፍጠር ያላትን አላማ አጠናክራ ትቀጥላለች ብለዋል።ሳቡ በተጨማሪም ሩሲያ የራሷን መንገድ የመምረጥ መብት ያላት ነፃ አገር እንደሆነች ተናግረዋል። በተጨማሪም ሩሲያ በአለም አቀፍ ደረጃ እና በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ውስጥ ትልቅ ሚና ትጫወታለች ብለዋል።ዜናውን በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፡- ለ iOS በአፕ ስቶር ለአንድሮይድ ስልኮች በዚህ APK ፋይል ሊንክ ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia