ኢትዮጵያ ከወርቅ ማዕድን 800 ሚሊዮን ዶላር ገቢ ለማግኘት አቅዳለችበተያዘው በጀት አመት ከማዕድን ዘርፍ 800 ሚሊዮን ዶላር የሚጠጋ ገንዘብ ለማግኘት መታቀዱን ተከትሎ ሶስት የወርቅ ማዕድን ፋብሪካዎች ግንባታ በፍጥነት እየተካሄደ መሆኑን የማዕድን ሚኒስቴር ዴኤታው ሚሊዮን ማቲዎስ ለኢፕድ ተናግረዋል።ፋብሪካዎቹ በቤንሻንጉል፣ በጋምቤላ እና በትግራይ ክልሎች የሚገኙ ሲሆን በሚቀጥሉት 18 ወራት ውስጥ ወደ ሥራ ይገባሉ። በዚህም የሀገሪቱ የወርቅ ምርት በዓመት 10 ቶን እንዲጨምር በማድረግ ከማዕድን ወጪ ንግድ የሚኘውን ገቢ ያሳድገዋል።በተጨማሪም በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ኩርሙክ ዲስትሪክት በዓመት ወደ ዘጠኝ ቶን የሚጠጋ ወርቅ ለማምረት መታቀዱን ገልፀዋል።የጉጂ ወርቅ ማዕድን ኩባንያ ከፍተኛ የፕሮጀክት ማስፋፊያ ላይ ሲሆን በአፋር ክልል የፖታሽ ማዕድን ልማት ፕሮጀክቶችን ለመጀመር መታቀዱንም አቶ ሚሊዮን አክለዋል።ሀገሪቱ በ2009 በጀት ዓመት 420 ሚሊዮን ዶላር ከማዕድን የወጪ ንግድ ገቢ ማግኘቷ ይታወቃል። መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፡- ለ iOS በአፕ ስቶር ለአንድሮይድ ስልኮች በGoogle Play ወይም በዚህ APK ፋይል ሊንክ ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia