የኡጋንዳ ጦር አዛዥ እና የደቡብ ሱዳን አቻቸው ትብብራቸውን ለማጠናከር ተስማሙ በኡጋንዳ መከላከያ ኃይል አዛዥ ጄኔራል ሙሁዚ ካይኔሩጋባ እና በደቡብ ሱዳን መከላከያ ኃይል አዛዥ ጄኔራል ሳንቲኖ ዴንግ ዎል መካከል ቅዳሜ እለት ውይይት ተካሂዷል። ውይይቱ "የጋራ በሆኑ ቀጠናዊ የጸጥታ ጉዳዮች" ላይ ያተኮረ እንደነበር የኡጋንዳ ጦር ገልጿል። ኡጋንዳውያን እና ደቡብ ሱዳናውያን "አንድ ህዝቦች ናቸው" ያሉት የደቡብ ሱዳን ጦር አዛዥ በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን ጥሩ ግኑኝነት አጽንኦት ሰጥተው አንስተዋል። ስብሰባው በቅርቡ በሁለቱ ሀገራት መካከል የተፈጠረውን የድንበር ግጭት ተከትሎ የተካሄደ ሲሆን ደቡብ ሱዳን የዩጋንዳ መከላከያ ሰራዊት ግዛቴን ጥሷል ስትል ከሳለች።ዜናውን በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፡- ለ iOS በአፕ ስቶር ለአንድሮይድ ስልኮች በGoogle Play ወይም በዚህ APK ፋይል ሊንክ ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia