እስራኤል በሊባኖስ የምታካሂደውን ጥቃት ተከትሎ 1 ሚሊዮን የሚጠጉ ሰዎቸ ተፈናቀሉ

እስራኤል በሊባኖስ የምታካሂደውን ጥቃት ተከትሎ 1 ሚሊዮን የሚጠጉ ሰዎቸ ተፈናቀሉ "በሊባኖስ ከቤታቸው የተፈናቀሉ ሰዎች ቁጥር ወደ 1 ሚሊዮን ደርሰዋል፤ ይህም በሊባኖስ ታሪክ ከፍተኛው የተስደተኞች ቁጥር" ነው ሲሉ የሊባኖስ ጠቅላይ ሚኒስትር ናጂብ ሚካቲ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ተናግረዋል። የሊባኖስ መንግሥት ለጋሽ ሀገራት ቤይሩትን እንዲረዱ ጥያቄ እንደሚያቀርብ እና ከእውቅ ለጋሾች ጋር በመተባበር አጠራጣሪ እርዳታዎች እንዳይገቡ እንደሚተባበር ጠቅላይ ሚኒስትሩ አክለዋል። ሚካቲ በሊባኖስ ንቅናቄ ሄዝቦላ እና በእስራኤል መካከል የተደረሰውን የተኩስ አቁም በተመለከተ የተባበሩት መንግሥታት የፀጥታው ምክር ቤት ያወጣውን ውሳኔ 1701 ተግባራዊ ለማድረግ ሀገራቸው ዝግጁ መሆኗን ገልጸዋል። ይህ እንዲሆን ምቹ ሁኔታዎች በተለይም በጋዛ ሰርጥ እንዲሁም በሁሉም የጦር ግንባሮች የተኩስ አቁም ሊደረግ ይገባል ብለዋል። እስራኤል በሊባኖስ እያካሄደች ያለውን ጥቃት ማስቆም የቤይሩት ቀዳሚ ጉዳይ መሆኑን ለማሳየት ሀገሪቱ ሁሉንም የፖለቲካ እና ዲፕሎማሲያዊ አቅም እንደምታንቀሳቅስ ሚካቲ አክለው ገልጸዋል። ይህ በእንዲህ እንዳለ በሊባኖስ ከሚገኙት እስላማዊ ቡድን መሪዎች መካከል አንዱ በጁብ ያኒን ከተማ በሚገኝ መኖሪያ ቤት ላይ በተፈጸመ ጥቃት ከቤተሰቡ ጋር እንደተገደለ ተዘግቧል።ዜናውን በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፡- ለ iOS በአፕ ስቶር ለአንድሮይድ ስልኮች በGoogle Play ወይም በዚህ APK ፋይል ሊንክ ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
Sputnik