እስራኤል በሊባኖስ የምድር ዘመቻ ሳትጀመር እንደማይቀር ዘገባዎች አመለከቱ

እስራኤል በሊባኖስ የምድር ዘመቻ ሳትጀመር እንደማይቀር ዘገባዎች አመለከቱ በድንበር አቅራቢያ የሊባኖሱን እንቅስቃሴ ይዞታዎች መደምሰስ ዓላማ ያለው አነስተኛ ዘመቻ ወይም "የድንበር አካባቢ የጦር እንቅስቃሴ" ከወዲሁ መጀመሩን አልያም በቅርቡ እንደሚጀመር የዩናይትድ ስቴትሱ ኤቢሲ ኒውስ የአሜሪካ ባለስልጣናትን ጠቅሶ ዘግቧል። ባለሥልጣናቱ ለጣቢያው እንደተናገሩት እስራኤል የምድር ኦፕሬሽኑን በተመለከተ የመጨረሻ ውሳኔ ላይ ባትደርስም ለዘመቻው ግን እየተዘጋጀች ነው። ባለስልጣናቱ ዘመቻው የሚጀመር ከሆነ በመጠኑ የተወሰነ የሚሆን ነው ብለዋል። በሰሜን እስራኤል የተፈናቀሉ ነዋሪዎችን ወደ መኖሪያቸው መመለስ የዘመቻው ቁልፍ ግብ እንደሆነም ባለስልጣናቱ አመልክተዋል። ሆኖም ይህንን ግብ ለማሳካት ናስራላን ማስወገድ በቂ አይደለም ሲሉ ተከራክረዋል። በተጨማሪ ዩናይትድ ስቴትስ እስራኤል በሊባኖስ ላይ ወታደራዊ ዘመቻ ለማካሄድ እየተዘጋጀች እንደሆነ የሚያሳዩ ምልክቶች እንዳሉ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን አስተዳደር ምንጭን እና ተጨማሪ የአሜሪካ ባለሥልጣንን ጠቅሶ ሲኤንኤን የዘገበ ሲሆን ዘመቻው የሚካሄድበት ጊዜ ግን እንዳልተጠቀሰ ጠቁሟል። የዩናይትድ ስቴትስ ግምገማ የምድር ጥቃቱን ለመጀመር የእስራኤል ወታደሮች መንቀሳቀስ እና አካባቢዎችን ማጥራት መጀመራቸውን መሰረት ያደረገ እንደሆነ ተገልጿል።ዜናውን በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፡- ለ iOS በአፕ ስቶር ለአንድሮይድ ስልኮች በGoogle Play ወይም በዚህ APK ፋይል ሊንክ ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
Sputnik
እስራኤል በሊባኖስ የምድር ዘመቻ ሳትጀመር እንደማይቀር ዘገባዎች አመለከቱ በድንበር አቅራቢያ የሊባኖሱን ንቅናቄ ይዞታዎች መደምሰስ ዓላማ ያለው አነስተኛ ዘመቻ ወይም "የድንበር አካባቢ የጦር እንቅስቃሴ" ከወዲሁ መጀመሩን አልያም በቅርቡ እንደሚጀመር የዩናይትድ ስቴትሱ ኤቢሲ ኒውስ የአሜሪካ ባለስልጣናትን ጠቅሶ ዘግቧል። ባለሥልጣናቱ ለጣቢያው እንደተናገሩት እስራኤል የምድር ኦፕሬሽኑን በተመለከተ የመጨረሻ ውሳኔ ላይ ባትደርስም ለዘመቻው ግን እየተዘጋጀች ነው። ባለስልጣናቱ ዘመቻው የሚጀመር ከሆነ በመጠኑ የተወሰነ የሚሆን ነው ብለዋል። በሰሜን እስራኤል የተፈናቀሉ ነዋሪዎችን ወደ መኖሪያቸው መመለስ የዘመቻው ቁልፍ ግብ እንደሆነም ባለስልጣናቱ አመልክተዋል። ሆኖም ይህንን ግብ ለማሳካት ናስራላን ማስወገድ በቂ አይደለም ሲሉ ተከራክረዋል። በተጨማሪ ዩናይትድ ስቴትስ እስራኤል በሊባኖስ ላይ ወታደራዊ ዘመቻ ለማካሄድ እየተዘጋጀች እንደሆነ የሚያሳዩ ምልክቶች እንዳሉ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን አስተዳደር ምንጭን እና ተጨማሪ የአሜሪካ ባለሥልጣንን ጠቅሶ ሲኤንኤን የዘገበ ሲሆን ዘመቻው የሚካሄድበት ጊዜ ግን እንዳልተጠቀሰ ጠቁሟል። የዩናይትድ ስቴትስ ግምገማ የምድር ጥቃቱን ለመጀመር የእስራኤል ወታደሮች መንቀሳቀስ እና አካባቢዎችን ማጥራት መጀመራቸውን መሰረት ያደረገ እንደሆነ ተገልጿል።ዜናውን በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፡- ለ iOS በአፕ ስቶር ለአንድሮይድ ስልኮች በGoogle Play ወይም በዚህ APK ፋይል ሊንክ ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia