ሩሲያ እና ዩክሬን ውይይት ማካሄድ የሚችሉበትን ሁኔት በአስቸኳይ መፍጠር እንደሚገባ የጊኒ ቢሳው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ተናገሩ

ሩሲያ እና ዩክሬን ውይይት ማካሄድ የሚችሉበትን ሁኔት በአስቸኳይ መፍጠር እንደሚገባ የጊኒ ቢሳው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ተናገሩ "ሩሲያና ዩክሬን የመነጋገር ግዴታ አለባቸው። ምክንያቱም ዛሬ ችግሩ በዩክሬን እና ሩሲያ ውስጥ ነው፤ ነገ ግን የሁላችንም ችግር ሊሆን ይችላል" ሲሉ የጊኒ ቢሳው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ካርሎስ ፒንቶ ፔሬራ ከተባበሩት መንግሥታት ጠቅላላ ጉባኤ ጎን ለጎን ከስፑትኒክ ጋር ባደረጉት ቆይታ ተናግረዋል። ጊኒ ቢሳው ግጭቱ በውይይት እና በፖለቲካዊ መንገድ ብቻ የሚፈታ እንደሆነ ታምናለች ሲሉም ሚኒስትሩ ጨምረው ገልጸዋል። "ጊዜ ማባከን አይገባም፤ በሩሲያ እና ዩክሬን መካከል ውይይት እንዲደረግ ሁኔታዎችን ማመቻቸት አስቸኳይ ነው" ብለዋል። ፔሬራ ከተመድ ጠቅላለ ጉባኤ ጎን ለጎን ከቻይና እና ብራዚል ባልደረቦቻቸው ጋር ስለ ሰላም ውጥኖች መወያየታቸውን ገልፀው አፍሪካም የውይይት ሀሳብ እንዳላት እና ወደፊት አንዳች ውጤት ያስገኛል የሚል እምነት እንዳላቸው ገልጸዋል።ዜናውን በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፡- ለ iOS በአፕ ስቶር ለአንድሮይድ ስልኮች በGoogle Play ወይም በዚህ APK ፋይል ሊንክ ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
Sputnik