በናይጄሪያ ቦርኖ ክልል ማይዱጉሪ ከተማ የደረሰው ከባድ የጎርፍ አደጋ ሁለት ሚሊዮን ሰዎችን አፈናቀለ “አብዛኛው ህዝባችን አሁንም ተፈናቅለው ያሉ ሲሆን መሰረተ ልማቶች በጎርፉ ፈራርሰዋል" ሲሉ የሰሜን ምስራቅ የቦርኖ ግዛት አስተዳዳሪ ባባጋና ዙሉም ለጎርፍ አደጋው የሚሆን 600 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ ላደረጉ የባንክ ሃላፊዎች ባደረጉት ንግግር ገልጸዋል። አስተዳዳሪው ድጋፉ የጎርፍ ተጎጂዎችን ለመርዳት ጥቅም ላይ እንደሚውል አረጋግጠው የገንዘብ፣ ምግብ እና አስፈላጊ ቁሳቁሶችን ጨምሮ እርዳታ ማከፋፈል መጀመሩን ተናግረዋል። የአፍሪካ ባለጸጋ ሰው አሊኮ ዳንጎቴን ጨምሮ ተቋማትና ግለሰቦችም ለእርዳታው አስተዋፅኦ አድርገዋል። የከተማዋ ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ የቆመ ሲሆን በርካቶች የደረሰባቸውን ጉዳት እና መፈናቀል ለመቋቋም እየታገሉ ነው ተብሏል። ቢያንስ የ40 ሰዎችን ህይወት የቀጠፈው ከባድ የጎርፍ አደጋ በርካቶችን በባዶ ቦታዎች፣ በሐይማኖት ተቋማት እና በ32 የተፈናቃይ ካምፖች፣ በህዝብ ትምህርት ቤቶችም ጨምሮ እንዲጠለሉ አስገድዷል።ዜናውን በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፡- ለ iOS በአፕ ስቶር ለአንድሮይድ ስልኮች በGoogle Play ወይም በዚህ APK ፋይል ሊንክ ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia