የማላዊ ፕሬዝዳንት ለአፍሪካ ሀገራት የዕዳ ሽግሽግ እና የብድር እፎይታ ጠየቁ "እዳችንን ለመቆጣጠር የተቻለንን ሁሉ እየሞከርን ነው፤ ሆኖም እዳዎቹን እንደገና ማሸጋሸግ ወይም አንዳንዶቹን እዳዎች ሙሉ በሙሉ ለመሰረዝ ብታስቡ አፍሪካ 'የመተንፈሻ ግዜ' ይኖራታል" ሲሉ ላዛሩስ ቻክዌራ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት 79ኛ ጉባኤ ላይ ተናግረዋል። ቀደም ሲል የአፍሪካ ልማት ባንክ ፕሬዝዳንት አኪንዉሚ አዴሲና ግልፅ ያልሆኑ ሀብትን መሰረት ያደረጉ ብድሮች የአፍሪካን የኢኮኖሚ እድገት እያደናቀፉ፣ የዕዳ ክፍያን የበለጠ አስቸጋሪ እያደረጉ እና የወደፊት እድገትን አደጋ ላይ አየጣሉ ነው ሲሉ አስጠንቅቀዋል። በአሁኑ ወቅት የአፍሪካ ሀገራት 65% የሚሆነውን የሀገር ውስጥ ምርታቸውን የውጭ ብድር ለመክፈል እንደሚያውሉም ጠቁመዋል።እንደ የዓለም ባንክ መረጃ የአፍሪካ የውጭ እዳ እ.አ.አ. በ2022 ከነበረው 1.12 ትሪሊዮን ዶላር በ2023 ወደ 1.152 ትሪሊየን ዶላር አድጓል።ዜናውን በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፡- ለ iOS በአፕ ስቶር ለአንድሮይድ ስልኮች በGoogle Play ወይም በዚህ APK ፋይል ሊንክ ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia