በናይጄሪያ 900 የሚጠጉ ህገ-ወጥ የነዳጅ ማጣሪያዎች መወገዳቸውን የሀገሪቱ መከላከያ ሚኒስቴር አስታወቀ የናይጄሪያ ጦር ኃይሎች በኒጀር ወንዝ ለሶስት ወራት ባካሄደው ዘመቻ 897 ህገ-ወጥ የነዳጅ ዘይት ማጣሪያዎችን በመለየት እንዳወደሙ እንዲሁም በድፍድፍ ዘይት ስርቆት የተሳተፉ 447 ሰዎችን በቁጥጥር ስር እንደዋሉ ሜጀር ጀነራል ኤድዋርድ ቡባ ተናግረዋል። ጦሩ 12 ሚሊየን ሊትር ድፍድፍ ዘይት እና 2.6 ሚሊየን ሊትር የተመረተ ናፍታ የወረሰ ሲሆን ምርቱን ለማጓጓዝ ጥቅም ላይ የዋሉ ከ100 በላይ መኪኖችን አወድሟል። ዘመቻው ከሰሃራ በታች ካሉ የአፍሪካ ሀገራት ትልቋ የነዳጅ አምራች በሆነችው ናይጄሪያ የነዳጅ ስርቆት መንሰራፋቱን ተከትሎ የመጣ ነው። የተሰረቀው ዘይት በህገ-ወጥ የነዳጅ ዘይት ማጣሪያዎች ተጣርቶ በጥቁር ገበያ እንደሚሸጥ ነው የሚገለጸው።ዜናውን በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፡- ለ iOS በአፕ ስቶር ለአንድሮይድ ስልኮች በGoogle Play ወይም በዚህ APK ፋይል ሊንክ ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia