የመስከረም 17 ረፋድ አበይት የዓለም ጉዳዮች፦ 🟠 የሩሲያ አየር መቃወሚያ 9 የዩክሬን ሰው አልባ አውሮፕላኖችን በአንድ ሌሊት ማውደሙን የሀገሪቱ መከላከያ ሚኒስቴር አስታወቀ። 🟠 የሩሲያ ውጭ ጉዳይ ሚንስትር ሰርጌ ላቭሮቭ ከተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሀፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ ጋር ከተመድ ጠቅላላ ጉባኤ ጎን ለጎን እንደተወያዩ የሩሲያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ገለጸ። 🟠 ቻይና፣ ብራዚል እና ሌሎች የደቡባዊ ዓለም ሀገራት የዩክሬንን ቀውስ ለመፍታት "የሰላም ወዳጆች" ክፍት መድረክ ለመፍጠር አስበዋል ሲሉ የቻይና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዋንግ ዪ ተናገሩ። 🟠 ቦሊቪያ ብሪክስ ታዳጊ ሀገራትን ለመለወጥ ይረዳል ብላ ስለምታምን ስብስቡን ትፈልገዋለች ሲሉ የቦሊቪያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ተናገሩ። 🟠 የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንታዊ እጩ ዶናልድ ትራምፕ አርብ ጠዋት ከቮልድሚር ዘለንስኪ ጋር ኒውዮርክ በሚገኘው ህንጻቸው እንደሚገናኙ አስታወቁ። 🟠 የእስራኤል አየር መከላከያ ሰራዊት ከየመን ተተኩሶ በቴል አቪቭ ድንጋጤ ፈጥሮ የነበረውን ሚሳኤል አጨናገፈ። 🟠 ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ የእስራኤል ተደራዳሪዎች የአሜሪካን የሊባኖስ ተኩስ አቁም ሃሳብ ሐሙስ ዕለት መወያየታቸውን እና በሚመጡት ቀናትም ስብሰባቸውን እንደሚቀጥሉ አስታወቁ።መረጃዎቹን በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፡- ለ iOS በአፕ ስቶር ለአንድሮይድ ስልኮች በGoogle Play ወይም በዚህ APK ፋይል ሊንክ ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia