ደቡብ አፍሪካ "አፓርታይድ በሌሎች ላይ ሲፈጸም ዝም ብላ አታይም"የደቡብ አፍሪካው ፕሬዝዳንት ሲሪል ራማፎሳ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤ ላይ ባደረጉት ንግግር የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በደቡብ አፍሪካ የነበውን የአፓርታይድ ስርዓት ለማስቆም የተጫወተውን ሚና አንስተው እስራኤል በፍልስጤማውያን ላይ እየወሰደች ያለችውን ድርጊት ከደቡብ አፍሪካ ልምድ ጋር ተመሳሳይነት ያለው እንደሆነ አንስተዋል፤ የእስራኤል እርምጃ ኮንነዋል። "ዘላቂው መፍትሄ ከእስራኤል ጎን ለጎን ምስራቃዊ እየሩሳሌም ዋና ከተማዋ የምትሆን የፍልስጤም መንግስት መመስረት ብቻ ነው " ሲሉ ራማፎሳ አሳስበዋል።ራማፎሳ የዜጎችን ስቃይ ለማስቆም በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ስርዓት እና በተለያዩ አለም አቀፍ ተቋማት በኩል አለም አቀፍ እርምጃ እንዲወሰድ እና ደቡብ አፍሪካ በእስራኤል ላይ በአለም አቀፉ ፍርድ ቤት የከፈተቸውን ክስ እንዲደግፍ ጠይቀዋል። የደቡብ አፍሪካው ፕሬዝዳንት አፍሪካ በተመድ የፀጥታው ምክር ቤት " መከባበርን መሰረት በማድረግ" ለመሳተፍና አስተማማኝነት ብሎም የተሻለ ዓለም እንዲኖር " ። የበኩሏን አስተዋፅኦ ለማድረግ ዝግጁ መሆኗን አፅንዖት ሰጥተው ተናግረዋል። በአህጉሪቱ ያለውን ግጭቶች ለመፍታት በተባበሩት መንግስታት ድርጅት እና በአፍሪካ ህብረት መካከል የበለጠ ትብብር እንዲኖርም አሳስበዋል።ዜናውን በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፡- ለ iOS በአፕ ስቶር ለአንድሮይድ ስልኮች በGoogle Play ወይም በዚህ APK ፋይል ሊንክ ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia