79ኛው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤ፡ የናይጄሪያ መከላከያ ሚንስትር ሀገሪቱ በፀጥታው ምክር ቤት መቀመጫ እንዲኖራት ጠየቁ"ናይጄሪያ ለአለም አቀፍ ሰላም ግንባታ እና ደህንነት ያላትን ቁርጠኝነት በማያሻማ መልኩ ማሳየት ቀጥላለች" ሲሉ መሃመድ ባዳሩ " መልቲ ላተራዝም ለዓለም አቀፍ ሰላም እና ደኅንነት " በሚል መሪ ቃል መጪው ጊዜ የመሪዎች ስብሰባ ላይ ተገኝተው ባደረጉት ንግግር ወቅት ተናግረዋል። ባዳሩ ናይጄሪያ በኮትዲቯር፣ በላይቤሪያ፣ በማሊ፣ በሱዳን እና በሌሎች ሀገራት የሰላም ማስከበር ተልእኮዎችን ጨምሮ በአፍሪካ እና በሌሎችም አካባቢዎች ሰላምን በማስጠበቅ ረገድ የተጫወተችውን ወሳኝ ሚና ገልጸዋል።ሚኒስቴሩ ሽብርተኝነትን እና ቀጣናዊ አለመረጋጋትን ለመዋጋት የአፍሪካ እግረኛ ጦር ሃይል ማጠናከር እንደሚያስፈልግ አሳስበዋል።ዜናውን በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፡- ለ iOS በአፕ ስቶር ለአንድሮይድ ስልኮች በGoogle Play ወይም በዚህ APK ፋይል ሊንክ ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia