ሂዝቦላህ በእስራኤል ወታደራዊ ካምፕ እና የፈንጂ ፋብሪካ ላይ ጥቃት አድርሻለሁ ብሏል "የእስላሚክ ሬዚስታንስ ተዋጊዎች ፋዲ-1 ሮኬቶችን በሰሜን ክልል የሚገኘውን ዋናው የአሞስ የሎጂስቲክስ ጦር ሰፈር ላይ ጥቃት ሰንዝሯል። ተዋጊዎቹ በሊባኖስ-እስራኤል ድንበር 60 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በፋዲ-2 ሮኬት በፈጸሙት ጥቃት በዝክሮን አካባቢ በሚገኘው የፈንጂ ፋብሪካ ላይ ጉዳት አድርሰናል። ” ሲል ንቅናቄው በመግለጫው አስታወቋል።በተጨማሪም ንቅናቄው ማክሰኞ ምሽት በእስራኤል አየር ሃይል አየር ማረፊያ ራማት ዴቪድ እና መጊዶ ላይ የሮኬት ጥቃት ፈጽሟል። "የእስላሚክ ሬዚስታንስ ተዋጊዎች በፋዲ-1 እና ፋዲ-2 ሮኬቶች ከአፉላ በስተምዕራብ በሚገኘው መጊዶ ወታደራዊ አየር ማረፊያ ላይ ጥቃት ፈፅመዋል። ተዋጊዎቹ ራማት ዴቪድ አየር ኃይል ጣቢያ እና አየር ማረፊያ ላይም የፋዲ-2 ሮኬቶች ተኩሰዋል" ሲል ንቅናቄው ገልጿል።መግለጫው ጥቃቱ የተፈፀመው "ሊባኖስን እና ህዝቦቿን ለመከላከል ነው" ብሏል።የእስራኤል አውሮፕላኖች በደቡባዊ እና በምስራቃዊ ሊባኖስ ሰፈሮች ላይ ሰኞ ማለዳ ላይ ከፍተኛ ጥቃት ማድረስ መጀመራቸው ይታወቃል። በደርዘን የሚቆጠሩ መንደሮች እና በርካታ ሰፈሮች ተጎድተዋል። የሂዝቦላህ ተዋጊዎች በበኩላቸው በደርዘን የሚቆጠሩ ሮኬቶችን ወደ ሰሜን እስራኤል ተኩሰዋል። የሊባኖስ መንግስት የተባበሩት መንግስታት በጉዳዩ ጣልቃ እንዲገባ እና የእስራኤልን ጥቃት እንዲያስቆም ከወዲሁ ጠይቋል።ቪዲዮዎች ከማህበራዊ ሚዲያ የተገኙ ናቸውዜናውን በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፡- ለ iOS በአፕ ስቶር ለአንድሮይድ ስልኮች በGoogle Play ወይም በዚህ APK ፋይል ሊንክ ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia