ቻይና እና ኢትዮጵያ በተለያዩ መስኮች ያላቸውን የሁለትዮሽ ትብብር ወደ ላቀ ደረጃ ለማሳደግ ተሰማምተዋልቻይና እና ኢትዮጵያ በሁሉም መስኮች ስትራቴጂካዊ አጋሮች ናቸው ያሉት የቻይናው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዩ ዋንግ ቻይና ከአፍሪካ ጋር በምታደርገው ትብብር የሁለትዮሽ ግንኙነት ግንባር ቀደምሥፍራ የሚሰጠው መሆኑን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ታዬ አፅቀ ስላሴ ጋር ባደረጉት ውይይት ወቅት ተናግዋል።ቻይናም ሆነች ኢትዮጵያ እንደ ዋና ታዳጊ ሀገራት እና ጠቃሚ የ‹‹ግሎባል ደቡብ› ሀገር አባልነታቸው›› የአንድ ወገን የበላይነትን በመቃወምና ፍትሃዊ የዓለም ሥርዓት እንዲሰፍን ቁርጠኛ መሆናቸውን ገልፀዋል፤ ሁለቱ ወገኖች በአለም አቀፍ እና አህጉር አቀፍ ጉዳዮች ላይ በቅንጅት እና በትብብርን በመስራት ለዓለም ሰላም እና ልማት የላቀ አስተዋፅኦ እንዲያበረክቱ አሳስበዋል።ኢትዮጵያ ከቻይና ጋር ያላትን ግንኙነት አወድሳ፤ የአንድ ቻይና ፖሊሲን በፅኑ እንደምትደግፍ ገልዋል።በአለም አቀፍ እና አህጉራዊ ጉዳዮች ኢትዮጵያ ከቻይና ጋር ያለውን ትብብር ለማጠናከር፣ የአንድ ወገን የበላይነትን በጋራ በመቃወም አለም አቀፍ ፍትሃዊነትን ለማስጠበቅ ፍቃደኛ መሆኗን ገልጸዋል። መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፡- ለ iOS በአፕ ስቶር ለአንድሮይድ ስልኮች በGoogle Play ወይም በዚህ APK ፋይል ሊንክ ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia