የመስከረም 13 ረፈድ ዋና ዋና የዓለም ዜናዎች 🟠 የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አወቃቀሮች የዘመናዊውን አለም ብዝሃነት በጉልህ የሚያንፀባርቁ መሆን አለባቸው፤ ለዚህም ተመድ ማሻሻል ያስፈልገዋል ሲሉ የደቡብ አፍሪካው ፕሬዝዳንት በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፅህፈት ቤት የወደፊቱ የመሪዎች ጉባኤ ላይ ተናገሩ። 🟠 የኬንያው ፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የፀጥታው ምክር ቤት እንዲሁም የአለም አቀፉ የፋይናንስ ሥርዓት ላይ የደቡብ ዓለም ሀገራትን ተሳቢ ባደረገ መልኩ ማሻሻያ እንዲደረግ በድጋሚ ጥሪ አቅርበዋል። 🟠 በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ የሚገኘው የተባበሩት መንግስታት የሰላም ማስከበር ተልዕኮ በታህሳስ 2024 ሀገሪቱን አይለቅም ሲሉ የመንግስታቱ ድርጅት የሰላም ማስከበር ስራዎች ምክትል ዋና ፀሀፊ ተናግዋል። አክለውም ታህሳስ 31 በሁሉም ወገኖች ዘንድ ይፋዊ ስምምነት እንዳልነበረው አስታውቀዋል።🟠 የማሊው ፕሬዝዳንት አሲሚ ጎይታ የሀገሪቱን የነፃነት በዓል ምክንያት በማድረግ ባደረጉት ንግግር የፀረ ሽብርተኝነት ትግሉን አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ቃል ገብተው ፤ በሀገሪቱ ሰላም፣ ደህንነት እና ልማት ለማምጣት ያላቸውን ቁርጠኝነት አረጋግጠዋል። 🟠 የሱዳን የጤና ጥበቃ ሚኒስትር የኮሌራ ወረርሽኝን ለመከላከል ለአንድ ወር የሚቆይ ዘመቻ መጀመሩን አስታውቀዋል። 🟠 የሩሲያው የኢነርጂ ሳምንት መድረክ ላይ የሩሲያው ፕሬዝዳንት ፑቲን ባደረጉት ንግግር በአዲሱ የጂኦፖለቲካዊ እውነታዎች በኢነርጂ ዘርፍ ያለው ትብብር ብሄራዊ ኢኮኖሚን ለማጠናከር ማገልገል እንዳለበት ጠቁመዋል። 🟠 በትላንትናው እለት በሩሲያ ቤልጎሮድ ግዛት የዩክሬን ጦር ሃይሎች በከፈቱት ጥቃት15 ሰዎች የቆሰሉ ሲሆን ከነዚህም ውስጥ ሁለቱ እጅግ በጣም አሳሳቢ ደረጃ ላይ እንደሚገኙ የአካባቢው ገዥ ግላድኮቭ ተናግረዋል።🟠 የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌይ ላቭሮቭ በኒውዮርክ በተካሄደው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤ ላይ በርካታ የሁለትዮሽ እና የባለብዙ ወገን ስብሰባዎችን እንደሚያካሂዱ የሩሲያ ተቀዳሚ ምክትል ቋሚ ተወካይ ፖሊያንስኪ አስታውቀዋል።🟠 ባይደን በመካከለኛው ምስራቅ እየተባባሰ ያለው ውጥረት እንዳሳሰበው ገልፀው፤ የዩናይትድ ስቴትስ አስተዳደር በአካባቢው ያለው ግጭት ወደ ጦርነት እንዳያመራ ለመከላከል የተቻለውን ሁሉ እንደሚያደርግ ገልፀዋል። 🟠 የዲሞክራቲክ እጩዋ ካማላ ሃሪስ ዓለማችንን ከሶስተኛው የአለም ጦርነት መከላከል እንደማይችሉ ትራምፕ ያምናሉ።ዜናውን በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፡- ለ iOS በአፕ ስቶር ለአንድሮይድ ስልኮች በGoogle Play ወይም በዚህ APK ፋይል ሊንክ ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia