የኬንያ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በሀገሪቱ ፖሊስ ምክትል ዋና ኢንስፔክተር ጀነራል ላይ አስተላልፎት የነበረውን የ6 ወራት እስራት አነሳጊልበርት ማሴንጌል የፍርድ ቤቱን ትዕዛዝ ባለማክበሩ ይቅርታ ጠይቋል። በነሀሴ ወር አጋማሽ ላይ በተደረጉ ፀረ-መንግስት ተቃውሞዎች ሶስት የፖለቲካ አንቂዎች መጥፋታቸውን በተመለከተ እንዲያስረዳ ፍረድ ቤቱ ቢያዝም ፤ ሰባት ጊዜ ፍርድ ቤት ባለመቅረቡ ጥፋተኛ ሆኖ ተገኝቷል። "ይህን የተከበረ ፍርድ ቤት ትእዛዝ በመጣሴ በትህትና ይቅርታ እጠይቃለሁ፤ እና ወደፊት ትእዛዙን ለመፈጸም ወስኛለሁ:: ፍርድ ቤት ያልተገኘሁት ሆን ብዬ ሳይሆን በተግባራዊ ሥራዎች ተግዳሮት የተነሳ ነው" ሲል ማሰንጌል ለፍርድ ቤቱ ተናግሯል።ፍርድ ቤቱ ማሴንጌል ፍርድ ቤት ላለመገኘቱ ያቀረበውን ማብራሪያ እንዲሁም መፀፀቱን በመጥቀስ የጠየቀውን ይቅርታ ተቀብሏል። ውሳኔው የተላለፈው ለአንድ ወር የጠፉት ሶስቱ አክቲቪስቶች ምንም ጉዳት ሳይደርስባቸው በህይወት ከተገኙ ከሰዓታት በኋላ ነው።ጉዳዩን ያቀረበው የኬንያ የህግ ሶሳይቲ የአክቲቪስቶቹ መሰወር ከአወዛጋቢው የፋይናንስ ህግ ጋር በተያያዘ በተቃውሞ ሰልፎች እና ቅስቀሳ ላይ ከመሳተፋቸው ጋር የተያያዘ ነው ሲል ተሟግቷል።ዜናውን በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፡- ለ iOS በአፕ ስቶር ለአንድሮይድ ስልኮች በGoogle Play ወይም በዚህ APK ፋይል ሊንክ ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia