ኡጋንዳ በአፍሪካ አህጉር ከሩሲያ ቁልፍ አጋሮች አንዷ እንደሆነች የሩሲያ ባለስልጣን ተናገሩ የሩሲያ ፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ-ጉባዔ ቫለንቲና ማትቪዬንኮ ከዩሬዢያ የሴቶች መድረክ ጎን ለጎን ከኡጋንዳ ምክትል ፕሬዝዳንት ጄሲካ አሉፖ ጋር ባደረጉት ውይይት የሩሲያ እና ኡጋንዳን ጠንካራ የፖለቲካ ግኑኝነት አድንቀዋል። ውይይቱ የንግድ እና ኢኮኖሚያዊ ግንኙነቶችን በማጠናከር ላይ ያተኮረ ሲሆን ማትቪዬንኮ የሩሲያ እና የኡጋንዳ በይነ መንግሥታት ኮሚሽን ውጤታማ ስራ አንስተዋል። አፈ-ጉባዔዋ ኢነርጂ፣ ግብርና፣ የሳይበር ደህንነት፣ ቴሌኮሙኒኬሽን እና ሌሎችንም ጨምሮ ለትብብር ተስፋ ሰጪ የሆኑ ዘርፎችንም ጠቁመዋል። ቫለንቲና ማትቪዬንኮ አክለውም “ሩሲያ እና ኡጋንዳ በዓለም አቀፍ ደረጃ ተባብረው ይሰራሉ” ያሉ ሲሆን ኡጋንዳ በአፍሪካ የሰላም ማስከበር ጥረት ውስጥ ያላትን ንቁ ሚና ጠቅሰዋል። አሉፖ በበኩላቸው ኡጋንዳ እና ሩሲያ ከ1960ዎቹ ጀምሮ የነበራቸውን ጠንካራ እና እያደገ ያለ ግንኙነት አንስተው አድንቀዋል።ዜናውን በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፡- ለ iOS በአፕ ስቶር ለአንድሮይድ ስልኮች በGoogle Play ወይም በዚህ APK ፋይል ሊንክ ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia